ቅጣቴን ፡ የተቀጣህልኝ
አበሳዬን ፡ ከእኔ ፡ ወሰድክልኝ (፪x)
ጌታ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱስ ፡ ተባረክልኝ
ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
פזמון: አንድ ፡ ወዳጅ (፪x) ፡ አለኝ
ለእኔ ፡ የሞተልኝ (፬x)
ሙግቴን ፡ ተሟግቶ ፡ አሸንፎልኛል
ጠላቴ ፡ እንዳይከሰኝ ፡ ነጻ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል
ይህን ፡ ወዳጄን ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ያልኩት
ከማንም ፡ አብልጬ ፡ በልቤ ፡ የሾምኩት
አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (፪x)
በምክሩ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይመልሳል
ከወዳጅ ፡ አብልጦ ፡ ወደ ፡ ልብ ፡ ይጠጋል
ደብቆ ፡ የያዘኝ ፡ እንዳልሆን ፡ የሌላ
የቅርቤ ፡ የምለው ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ
አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (፪x)